top of page
Image by Greg Rosenke

ProZ Pro Bono በጨረፍታ

ይህ ድርጣቢያ በአብዛኛው በእንግሊዝኛ ነው፣ ነገር ግን በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀገራት የሚገኙ ጓደኞቻችን እና ደንበኞቻችን ስለ ፕሮግራሙ በራሳቸው ቋንቋ እንዲያውቁ እድል መስጠት እንፈልጋለን። ከታች ያለው ገጽ ፕሮጀክቱን፣ የተሳተፉትን ሰዎች እና አነሳሱን ይዳስሳል። የተተረጎመው በአንዳንድ ኮከብ በጎ ፈቃደኞቻችን ነው። እና እባክዎ እርስዎም በማንኛውም ቋንቋ ሊጽፉልን እንደሚችሉ እና በተመሳሳይ ቋንቋ እንደምንመልስልዎ ልብ ይበሉ።

ምን ፣ ማን ፣ መቼ ፣ የት ፣ ለምን?

ምን?
ProZ Pro Bono ፕሮግራም በዓለም ትልቁ የፕሮፌሽናል ተርጓሚዎችና አስተርጓሚዎች ማህበረሰብ በሆነው ProZ.com የተከፈተ ከገንዘብ ነጻ የሆነ የበጎ አድራጎት ተነሳሽነት ነው። ይህ ፕሮግራም የቋንቋ ባለሙያዎችን የትርጉም እና የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ከሚፈልጉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ያገናኛል፣ ሁሉነገሩ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ። በዚህ ፕሮግራም፣ ProZ.com ዓለም አቀፋዊ የቋንቋ ድጋፍ መረብን ያመቻቻል፣ ይህም አገልግሎት በቂ አገልግሎት ላላገኙ ማህበረሰቦች አስፈላጊ መረጃዎችን እና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል።

ማን?

የProZ Pro Bono ፕሮግራም በዓለም ዙሪያ ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ያገለግላል፤ ይህም የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰቦችን መድረስ እንዲችሉ እና ውስን ሀብታቸውን አቅመ ደካሞችን የማገልገል ዋና አላማቸው ላይ እንዲያውሉ ያደርጋቸዋል። የትርጉም እና የማስተርጎም ስራው የሚከናወነው የProZ.com የተመዘገቡ አባላት በሆኑ የቋንቋ ባለሙያዎች ነው። እነዚህ ግለሰቦች እውቀታቸውን እርዳታ ለሚሹ ሰዎች በነጻ በማቅረብ አዎንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። በProZ.com አባላት ፈንድ የተደረገ ነው።

የት?

የProZ Pro Bono ፕሮግራም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰራ ነው። ከሁሉም የዓለም ማዕዘናት የተውጣጡ የቋንቋ ባለሙያዎች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ። ፕሮግራሙ የድንበር ተሻጋሪ ትብብርን በማስቻል የ ProZ.com ምናባዊ ተፈጥሮን ይጠቀማል። በጎ ፈቃደኞች አገልግሎቶቻቸውን ሊሰጡ ይችላሉ እና ተጠቃሚዎች ጂኦግራፊያዊ አካባቢያቸው ምንም ይሁን ምን እገዛ መጠየቅ ይችላሉ።

 

መቼ?

የProZ Pro Bono ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ተነሳሽነት ነው፣ እና ዓመቱን ሙሉ መሳተፍ ይቻላል። የቋንቋ ባለሙያዎች በማንኛውም ጊዜ እንደ በጎ ፈቃደኞች መመዝገብ ይችላሉ፣ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ወይም መሻቱ ያላቸው ግለሰቦች አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ። በጊዜ አጠቃቀም ውስጥ ያለው ተለዋዋጭነት ከቋንቋ ጋር ለተያያዙ አስቸኳይ ፍላጎቶች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል።

ለምን?

የProZ Pro Bono መርሃ ግብር አስፈላጊ የሆኑ የመረጃዎች እና አገልግሎቶች መዳረሻዎችን ለማቅረብ ወይም ለማግኘት ለሚጣጣሩ አካላት የቋንቋ ክፍተቶችን የማጥበብ ወሳኝ ዓላማን ያሳካል። በትርጉም እና ማስተርጎም ማህበረሰብ ውስጥ ትብብርን እና ድጋፍን ማጎልበት እንዲሁም በዓለም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ከሚሉት የProZ.com ዋና እሴቶች ጋር ይጣጣማል።. ይህ ፕሮግራም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤን፣ ተግባቦትን እና የመረጃ ተደራሽነትን የማስተዋወቅ ሰፋ ያለ ተልዕኮን ያሟላል።

 

መርሃግብሩ የቋንቋ ባለሙያዎች ችሎታቸውን በበጎ ፈቃደኝነት በዓለም ዙሪያ ለተቸገሩ ወሳኝ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ የሚያስችል ርህራሄ እና ተፅእኖ ያለው ጥረት ነው።  በProZ Pro Bono ፕሮግራም ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ተርጓሚዎች እና አስተርጓሚዎች ችሎታቸውን እና እውቀታቸውን የሚያበረክቱት ለግል ጥቅማቸው ሳይሆን የቋንቋ ድጋፍ በሚፈልጉ ሰዎች ህይወት ላይ በጎ ተጽእኖ ለመፍጠር ነው።

Translated by Yidnekachew Geremew / በይድነቃቸው ገረመው ተተረጎመ

bottom of page